የሆሳዕና መንበረ ጵጵስና ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ታቦት ከሰሜን ሸዋ መንዝ ግሼ አውራጃ ጠራ ከተባለ አካባቢ በ1887 ዐ.ም በራስ ጎበና ዳጮ አማካኝነት መጥታ በሌሞ ወረዳ አና በተባለ ቦታ በግዜያዊነት አረፈች።
ራስ ጎበና ዳጮ በዐጼ ምንሊክ ለአድዋ ጦርነት ጥሪ ተደርጎላቸው ከግዛታቸው ሲሄዱ በምትካቸው የተሾሙት ራስ አባተ ቧ ያለው ታቦተ ማርያምን በ1901 ዐ.ም ወደ ሆሳዕና በማምጣት አሁን በምትገኝበት ቦታ ላይ የሳር ክዳን ቤተመቅደስ በማሰራት ቀዳሴ ቤቱ ከበረ።
ከ106 ዓመታት በላይ አገልግሎት የሰጠችው ይህች ጥንታዊት ቤተክርስቲያን ለሁለተኛ ጊዜ የካቲት 21/2007 ዓ.ም በተነሣ ቃጠሎ ብትወድምም ጽላቱ ምንም ሳይቃጠል በክብር ወጥቷል። አዲሱን ህንጻ ለመገንባት የበኩሉዎን አስተዋጽኦ ያድርጉ።
የንግድ ባንክ አካውንት፦ 1000110719969 (ባቴና ቅርንጫፍ)
ስልክ፦ 0912-446829 / 0913-750229
የሀገረስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ እና የሰንበት ት/ቤቱ ሊቀመንበር
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሀዲያና ስልጤ ሀጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል::
የአንተ ሃላፊነት መብራቱን ማብራት ብቻ ነው ጨለማውም በራሱ ጊዜ ይጠፋል፡፡
የሆሳዕና መንበረ ጵጵስና ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ።
የሆሳዕና መንበረ ጵጵስና ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ፈለገ ህይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሊቀ መንበር፡፡
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል በደብራችን ታላቅ መንፈሳዊ ሥርዓት ይከበራል።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ወደ ኢየሩሳሌም የገባበትን መታሰቢያ በታላቅ ዝማሬና ድምቀት እናከብራለን።
በቀደሙት ዓመታት በደብራችን በታማኝነት ሲያገለግሉ የነበሩ የሃይማኖት አባቶችና መሪዎች ታሪክና አሰረ-ፍኖት